ኮቪድ/COVID-19 ክትባቶች

ክትባቶች መውሰዱ ከCOVID-19 ቫይረስ ይከላከለልናል። አውስትራሊያ ውስጥ እድሜው 5 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ እያንዳንዱ ሰው በነጻ ለCOVID-19 ክትባት መውሰድ ቀጠሮ ማቀናጀት ይችላል።.

ስለ COVID-19 ክትባቶች

በአውስትራሊያ እያንዳንዱ እድሜው 5 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ እንዲሁም ከ6 ወር እስከ 4 ዓመት እድሜ ያላቸው የተወሰኑ ህጻናት ለCOVID-19 ክትባት መውሰድ ብቃት አላቸው።

ክሊኒክ ማግኘት እና ቀጠሮ ማስያዝ

COVID-19 ክትባቶች በአውስትራሊያ ውስጥ ለሁሉም ሰው ያለክፍያ በነጻ ናቸው። ይህም የMedicare ካርድ የሌላቸው ሰዎች፤ የውጭ አገር ጎብኚዎች፤ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች፤ ስደተኛ ሠራተኞች እና ጥገኝነት ፈላጊዎችን ያካትታል።

ክትባት ማግኘት እርስዎን፤ ቤተሰብዎን እና ማህበረሰብዎን ከ COVID-19 ለመጠበቅ ይረዳል።

በአውስትራሊያ መንግሥት ክትባት የማድረግ ግዴታ ስላልተደረገባችሁ ከCOVID-19 በመከላከል ላይ ክትባት ላለመውሰድ መምረጥ ትችላላችሁ።

አንዳንድ የክልልና ተሪቶርይ አስተዳደር ህዝባዊ የጤና አጠባበቅ ትእዛዞች በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ክትባትን በመውሰድ መከላከል ግዴታ ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል ለአንዳንድ የሥራ ዓይነቶችና ለአንዳንድ ማህበረሰባዊ እንቅስቃሴዎች።

ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው

COVID-19 ክትባት መውሰድ ድህንነቱ አስተማማኝ እና የሰዎችን ህይወት ያተርፋል። በአውስትራሊያ ህክምና ጥራት አስተዳደር/Therapeutic Goods Administration (TGA) ለCOVID-19 የክትባት ደህንነት እና የጎንዮሽ ጉዳቶችን በቅርበት መከታተሉን ቀጥሏል።

በአውስትራሊያ ስለሚቀርብ እያንዳንዱ ክትባት ተጨማሪ ማወቅ፡

ክትባት ካገኙ በኋላ ጥያቄ ወይም ጭንቀት ካለብዎት የክትባት ክሊኒክዎን ወይም ሀኪምዎን ያነጋግሩ።

ማን ክትባት ማግኘት አለበት

እያንዳንዱ እድሜው 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ ሰው በ COVID-19 ላይ ክትባት ማግኘት አለበት።

በ COVID-19 በጠና ከመታመም ወይም ከመሞት ለመከላከል የተሻለ ጥበቃ ለማግኘት ለእድሜዎ እና ለጤናዎ የሚያስፈልግዎትን የታዘዘ መጠን/doses ክትባቶችን መውሰድ ይኖርብዎታል።

እድሚያቸው ከ6 ወር እስከ 4 ዓመት ለሆኑት አንዳንድ ልጆች COVID-19 ክትባት ለመውሰድ የሚፈቀድላቸው፡

 • ከባድ የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም ላለባቸው
 • የአካል ጉዳት ወይም
 • በከባድ COVID-19 የመያዝ እድላቸውን ከፍ የሚያደርጉ ውስብስብ እና/ወይም በርካታ የጤና እክሎች ያለባቸው ሰዎች ናቸው።

እድሜያቸው ከ6 ወር እስከ 4 ዓመት የሆኑ ህጻናት ማግኘት ያለባቸው፡

 • ሁለት የመጀመሪያ ጊዜ መጠን/doses የCOVID-19 ክትባት
 • ከባድ የበሽታ መከላከል አቅም ያላቸው ከሆነ ሶስተኛ የመጀመሪያ ጊዜ መጠን/doses ይሆናል።

እድሜያቸው ከ5 እስከ 17 ዓመት የሆኑ ልጆች ማግኘት ያለባቸው፡

 • ሁለት የመጀመሪያ ጊዜ መጠን/doses የCOVID-19 ክትባት
 • ከባድ የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም ያላቸው ከሆነ ሶስተኛ የመጀመሪያ ጊዜ መጠን/doses ነው።
 • የማበረታቻ መጠን/doses የሚያስፈልግ፡
  • ከባድ የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም ላለባቸው ሰዎች
  • አካል ጉዳተኛ ለሆኑ
  • በከባድ COVID-19 የመያዝ እድላቸውን የሚጨምሩ ውስብስብ እና/ወይም ብዙ የጤና ሁኔታዎች ላሏቸው
  • የመጨረሻ መጠን/dose ክትባትን ወይም በCOVID-19 በሽታ መያዝ ከተረጋገጠ በኋል 6 ወራት ካለፈ ይሆናል።

ልጅዎ የማበረታቻ መጠን ክትባትን ስለመወሰን ሀኪምዎ ሊረዳዎ ይችላል።

እድሜው 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ሰው ሁሉ ማግኘት ያለበት፡

 • ሁለት የመጀመሪያ ጊዜ የCOVID-19 ክትባት
 • ከባድ የበሽታ መከላከል አቅም ያላቸው ከሆነ ሶስተኛው የመጀመሪያ ጊዜ ክትባት

እድሜያቸው 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሁሉ የመጨረሻ መጠን/dose ክትባትን ከወሰዱ ወይም የተረጋገጠ በCOVID-19 በሽታ መያዝ ከተረጋገጠ በኋላ 6 ወራት ካስቆጠረ የማበረታቻ መጠን/dose ክትባትን እንዲወስዱ ግምት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

ስለ COVID-19 ማበረታቻ ክትባት ምክር በተጨማሪ ማወቅ፡

ህጻናት

ከኦስቫክስሴፍቲ የተገኘ COVID-19 የክትባት ደህንነት ጥሬ መረጃ እንደሚያሳየው እድሚያቸው ከ5 እስከ 15 ዓመት ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናት COVID-19 ክትባትን ከወሰዱ በኋላ ከዚህ ቀጥሎ ባሉት ቀናት የጎንዮሽ ጉዳት እንደሚደርስባቸው ሪፖርት ተደርጓል።

COVID-19 ክትባቶችን በመውሰድ ወደፊት በልጆች ላይ መካንነት እንደሚያስከትሉ የሚያሳይ ምንም ማስረጃ የለም።

ለልጆች እና ለአፍላ የጉርምስና እድሜ ላይ ስለ COVID-19 ክትባቶች ላሉት በበለጠ ማወቅ

ነፍሰ ጡር ወይም ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች

COVID-19 ክትባቶች እርጉዝ፤ ጡት ማጥባት፤ ወይም ለእርግዝና እቅድ ካለዎት ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው። በማንኛውም የእርግዝና ወቅት ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ።

ስለ እርግዝና፣ ጡት ማጥባት፣ እና COVID-19 ክትባቶች በበለጠ መማር ማወቅ።

የአካል ጉዳተኛ ሰዎች

የአካል ጉዳተኛ የሆኑ ሰዎች በCOVID-19 ከባድ ህመም የመያዝ አጋጣሚያቸው ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ክትባት ሊሰጣቸው ይገባል።

ተጨማሪ እርዳታ ወይም ድጋፍ ከፈለጉ የአካል ጉዳተኝነት መግቢያ እርዳታ ነስመር/Helpline በስልክ 1800 643 787 መደወል ይችላሉ። ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ።

አስተርጓሚ ካስፈለገዎት የትርጉምና አስተርጓሚ አገልግሎት በስልክ 131 450 ይደውሉ እና ለአካል ጉዳተኛ መግቢያ ስልክ እንዲደውሉ ጠይቋቸው።

አሁን የጤና ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች

በአሁኑ ጊዜ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በCOVID-19 የሚከሰት ከባድ ህመም የመያዝ አጋጣሚያቸው ሰፊ ከመሆኑም በላይ ክትባት ሊሰጣቸው ይገባል።

ባለዎት ሁኔታ በጣም ጥሩ የሆነ ክትባትን በተመለከተ ከመደበኛ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ጋር ይነጋገራሉ።

ክትባት የት ነው ስለሚገኝ

COVID-19 ክትባት ማግኘት የሚችሉት፡

 • በኮመንዌልዝ ክትባት መስጫ ክሊኒኮች
 • በተሳትፎ አጠቃላይ ሀኪሞች
 • በአቦርጅኖች መቆጣጠሪያ ማህበረሰብ ጤና ጥበቃ አገልግሎቶች
 • በአስተዳደር ክልል ወይም ተሪቶርይ ክትባት መስጫ ክሊኒኮች፣ እና
 • በተሳታፊ መድኃኒት ቤቶች ይሆናል።

አጠቃላይ ሀኪሞች ለክትባቱ ማስከፈል አይችሉም።

በአካባቢዎ ክትባት መስጫ ክሊኒክዎን ለማግኘት እና ለክትባትዎ ቀጠሮ ለመያዝ Vaccine Clinic Finder ይጠቀሙ።

በክትባት ቀጠሮዎ ላይ በስልክ ወይም በአካል ቀርቦ መተርጎም ካስፈለገዎ ለትርጉምና አስተርጓሚ አገልግሎት በስልክ 131 450 ይደውሉ።

EVA፤ እንዲሁም (በቀላሉ ክትባት ማግኘት/Easy Vaccine Access) በመባልም የሚታወቀውን አገልግሎት በቋንቋዎ በስልክ የCOVID-19 ክትባት ቀጠሮ ለማስያዝ የሚረዳ አገልግሎት ነው። EVA የሚሰራው ከጥዋቱ 7am ሰዓት እስከ ምሽቱ 10pm ሰዓት (AEST)፣ በሳምንት 7 ቀናት ነው። ስለ EVA የበለጠ ለማወቅ ጥረት ማድረግ።

የ Medicare ካርድ ከለለዎት

የ Medicare ካርድ ከሌለዎት ከማህበረሰብ ፋርማሲዎች እና ከአስተዳደር ክልል ወይም ተሪቶርይ ክትባት መስጫ ክሊኒኮች (አሁንም በሥራ ላይ ያሉበት) ያለክፍያ በነጻ ክትባትዎን ማግኘት ይችላሉ።

ከCOVID-19 ክትባትዎ በፊት

ቀደም ሲል ቀጠሮ ካላስያዙ.

ክሊኒክ ማግኘት እና ቀጠሮ ማቀናጀት

የ Medicare ካርድ ካለዎት ዝርዝር መረጃዎን ወቅታዊ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ፦

ከቀጠሮዎ በፊት ወይም ለሌላ ሰው የክትባት ውሳኔ የሚያደርጉ ከሆነ የስምምነት መስጫ ቅጽን እንዲሞሉ ሊጠየቁ ይችላሉ።

ስምምነት መስጫ ቅጽን ያንብቡ።

እድሚያቸው ከ5 እስከ 11 ዓመት ለሆኑ ልጆች መረጃና ስምምነት መስጫ ቅጽ ያለን ያንብቡ።

ከእርስዎ COVID-19 ክትባት በኋላ

አልፎ አልፎ አለመስማማት አለርጂ ቢያጋጥምዎ ክትባት ከወሰዱ በኋላ ቢያንስ ለ15 ደቂቃ ክትትል ይደረግልዎታል። ክትባቱን የሚሰጥዎ ሰው ወዲያውኑ ምላሽ እንዲሰጥ ሥልጠና ተሰጥቷል።

አብዛኛውን ጊዜ ከ COVID-19 ክትባቶች የሚከሰቱ ችግሮች ቀላል እና ከ 1 እስከ 2 ቀናት ውስጥ ይጠፋሉ። በተለመዱ ሊፈጠር የሚችል ችግር የጎንዮሽ ጉዳቶች የሚካተቱት፡

 • መርፌው በገባበት ክንድ ላይ ህመም
 • ድካም መንፈስ
 • እራስ ምታት
 • የጅማት ህመም
 • ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት

እንደ ማንኛውም መድሃኒት ወይም ክትባት፣ አልፎ አልፎ የሚከሰት ወይም ያልታወቁ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ከባድ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳለብዎ ከተሰማዎት ከጤና ጥበቃ ባለሞያዎ ወይም ከአገር አቀፍ ኮሮናቫይረስ እርዳታ መስመር ጋር መገናኘት።

ስልክ 1800 020 080

አስተርጓሚ ካስፈለገዎት ወደ አገር አቀፍ ኮሮናቫይረስ እርዳታ መስመር/Helpline ይደውሉ እና አማራጭ ቁጥር 8’ን ይምረጡ።

የክትባት መውሰድ ማረጋገጫ

የ COVID-19 ክትባትዎን ማረጋገጫ ማግኘት የሚችሉት የእርስዎን የበሽታ መከላከያ ክትባት ጽሁፋዊ መግለጫ ሲያቀርቡ ነው።

የእርስዎን የበሽታ መከላከያ ክትባት ጽሁፋዊ መግለጫ ማግኘት የሚችሉት፡

የ Medicare ካርድ ከሌለዎት ወይም myGov አካውንት መጠቀም ካልቻሉ፤ የእርስዎን በሽታ መከላከያ ክትባት ጽሁፋዊ መግለጫን ማግኘት የሚችሉት፡

 • የክትባት አቅራቢዎን አንድ ቅጂ እንዲያትምላችሁ በመጠየቅ
 • የአውስትራሊያ በሽታ መከላከያ ክትባት ምዝገባ/ሬጅስትራር ጥያቄ ማቅረቢያ መስመር በስልክ 1800 653 809 አድርጎ (ከጥዋቱ 8 am – 5 pm ከሰኞ እስከ ዓርብ AEST) በመደወል ጽሁፋዊ መግለጫዎን በፖስታ እንዲላክልዎት በመጠየቅ ነው። በፖስታ ቤት ለመድረስ እስከ 14 ቀናት ሊፈጅ ይችላል።

የCOVID-19 ክትባትዎን እንዴት ማስረጃ ማግኘት እንደሚቻል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በድረገጽ Services Australia website ላይ ይመልከቱ።

የት እንደሚሄዱ የታመኑ መረጃ

አስተማማኝ እና በህጋዊ ምንጮች አማካኝነት ስለ COVID-19 እና ስለ COVID-19 ክትባት መስጫ ፕሮግራም እያወቁ መቆፐት ጠቃሚ ነው።

በ COVID-19 ክትባቶች ላይ ለሚነሱ የተለመዱ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ይቻላል በ 63 ቋንቋዎች

ስለ COVID-19 ክትባቶች በቋንቋ የተዘጋጁ መገልገያዎችን የያዘ መረጃ ፓኬት ይገኛል።

ስለ COVID-19 በቋንቋዎ መረጃን ያንብቡ።

መገልገያዎች

ተጨማሪ የተተረጎመ COVID-19 የክትባት መረጃን ይመልከቱ።

Date last updated:

Help us improve health.gov.au

If you would like a response please use the enquiries form instead.