ስለ COVID-19 ክትባቶች

አውስትራሊያ ውስጥ እድሜው 5 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆነ እያንዳንዱ ሰው ለክትባት መስጫ ቀጠሮ ማቀናጀት ይችላሉ።

ክሊኒክ ማግኘትና ቀጠሮ ማስያዝ

አውስትራሊያ ውስጥ ለእያንዳንዱ ሰው የCOVID-19 ክትባቶች በነጻ ነው። በዚህ የሚካተት የMedicare ካርድ ለሌላቸው፤ የውጭ አገር ጎብኝዎችን፤ ያአለም አቀፍ ተማሪዎችን፤ ማይግራት/መጤ ሰራተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ይሆናል። ክትባትን መውሰዱ ለራስዎ፤ ቤተሰብዎ እና ማህበረሰብዎ ከCOVID-19 ለመከላከል ይረዳል።

የአውስትራሊያ መንግሥት ለክትባት መውሰድ ግዴታዊ ስላላደረገው ታዲያ ከCOVID-19 ለመከላከል ክትባትን መውሰዱን መምረጥ ይችላሉ።

በአንዳንድ አስተዳደር ክልል እና ተሪቶርይ ህዝባዊ ጤና ጥበቃ ትእዛዝ በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ክትባትን መውሰዱ ግዴታ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፡ በአንዳንድ የሥራ ዓይነቶች እና በአንዳንድ ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ሥራዎች ላይ

ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው

የCOVID-19 ክትባት መውሰድ ደህንነቱ የተጠበቀና ህይወትን ያድናል። አውስትራሊያ ውስጥ የ Therapeutic Goods Administration (TGA) በቅርበት ሆኖ ለCOVID-19 ክትባት ደህንነት እና ሊከሰት በሚችል ችግር ላይ ቀጣይ ቁጥጥር ክትትል ያደርጋል።

አውስትራሊያ ውስጥ ስለሚቀርብ እያንዳንዱ ክትባት በበለጠ መማር:

ከቫይረስ ጋር በቅርበት ሲገናኙ፤ ሰውነትዎ ቫይረሱን እንዲያስወግድ COVID-19 ክትባቶች ያስተምራሉ።

ክትባቱን ከወሰዱ በኋላ ማንኛውም ጥያቄዎች ወይም አሳሳቢ ጉዳይ ካለዎት ለርስዎ ክትባት ሰጪ ክሊኒክ ወይም ሀኪም ያነጋግሩ።

በበለጠ መማር ስለክትባትዎን ከወሰዱ በኋላ ምን እንደሚጠበቅ።

ማነው ክትባት ማግኘት ያለበት

እድሜው 5 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ እያንዳንዱ ሰው ከCOVID-19 መከላከያ ክትባትን መውሰድ አለባቸው።

የCOVID-19 ክትባትን መውሰዱ በ COVID-19 ከሚፈጠር ከባድ ህመም ወይም መሞት ይከላከልዎታል።

እንዲሁም ክትባትን ማግኘቱ የቫይረስ ስርጭትን በማዳከም በአካባቢዎ ያሉትን ሰዎች ለመከላከል ይረዳሉ።

ያለዎትን COVID-19 ክትባት አወሳሰድ ወቅታዊ እንደሆነ ግምት ውስጥ የሚገባው በእርስዎ እድሜና ጤና ፍላጎት ለተመከሩት መጠን/doses ክትባቶች በሙሉ መውስድ አለብዎ።

እድሜያቸውከ5 እስከ 15 ዓመት ያሉ ህጻናት ማግኘት ያለባቸው:

 • የመጀመሪያ ጊዜ መጠን/dose 1 እና 2 የCOVID-19 ክትባት
 • ከባድ የበሽታ መቋቋም ሀይላቸው ለተዳከመ የመጀመሪያ ጊዜ መጠን/dose 3

እድሜው 16 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆነ እያንዳንዱ ሰው ማግኘት ያለበት:

 • የመጀመሪያ ጊዜ መጠን/dose 1 እና 2 የCOVID-19 ክትባት
 • ከባድ የበሽታ መቋቋም ሀይላቸው ለተዳከመ የመጀመሪያ ጊዜ መጠን/dose 3
 • ለCOVID-19 ክትባት የማበረታቻ ተጨማሪ መጠን/dose።

እንዲሁም ለ COVID-19 የክረምት መጠን/dose ክትባትን መውሰድ ያለብዎት፤ የማበረታቻ መጠን/dose ክትባትዎን ከወሰዱ 4 ወራት ከሆነና እርስዎ።

 • እድሜዎ 65 ዓመት ወይም ከዚህ በላይ
 • በእድሜ አንጋፋ እንክብካቤ መስጫ ወይም ለአካለ ጕዳተኛ እንክብካቤ ምስጫ መገልገያ ላይ ነዋሪ ከሆኑ
 • በእድሜ አንጋፋ እንክብካቤ መስጫ ወይም ለአካለ ጕዳተኛ እንክብካቤ ምስጫ መገልገያ ላይ ነዋሪ ከሆኑ
 • እድሜዎ 50 ዓመት ወይም ከዚህ በላይ እና አቦርጂናል ወይም ቶረስ ስትራት አይላንደ ተወላጅ ከሆኑ ነው።

በምርመራ ውጤት COVID-19 ከተገኘብዎት የሚቀጥለውን የCOVID-19 ክትባት መጠን/dose ከመውሰድዎ በፊት 3 ወራት እንዲጠብቁ ይመከራል።

ሰዎች የማበረታቻ መጠን/dose ክትባታቸውን ከወሰዱ በኋላ COVID-19 ከያዛቸው ለክረምት መጠን/dose ክትባትን ከመውሰዳቸው በፊት ቢያንስ ለ 3 ወራት መጠበቅ አለባቸው።

ያለዎትን COVID-19 ክትባቶች ወቅታዊ አድርጎ መቆየቱ ጠቃሚ ነው። የተለያዩ ሰዎች ለተለያየ የCOVID-19 ክትባቶችን በተለያየ ጊዜያት መውሰድ ሊያስፈልጋቸው ይችል ይሆናል። እርስዎ እና ቤተሰብዎ ክትባትዎን ወቅታዊ እንዲሆን ምን ማድረግ እንዳለብዎ ለእርስዎ ጤና ጥበቃ አቅራቢ ያነጋግሩ።

ህጻናት

ለህጻናት COVID-19 ክትባቶች ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

ህጻናት ክትባትን በመውሰድ ቫይረሱ ወደ ታዳጊ ወንድምና እህቶች፤ አያቶች እና ወደ ሰፊው ማህበረሰብ እንዳይተላለፍ ለመርዳት ይችላሉ።

በበለጠ መማር ስለ ህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች የCOVID-19 ክትባቶች።

እርጉዝ ወይም ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች

ወይም ለማርገዝ እቅድ ለሚያወጡ ሴቶች የCOVID-19 ክትባቶችን መውሰዱ ድህንነቱ የተጠበቀ ነው። በማንኛውም እርግዝና ደረጃ ጊዜ ክትባትን መውሰድ ይችላሉ።

በበለጠ መማር ስለ እርጉዝና፤ ጡት ስለማጥባት እና COVID-19 ክትባቶች።

አካለ ጉዳተኛ ለሆኑ ሰዎች

አካለ ጉዳተኛ የሆኑ ሰዎች በCOVID-19 የተነሳ ከባድ ህመም ችግር ስለሚያጋጥማቸው እና ክትባት ማግኘት አለባቸው።

በበለጠ እርዳታ ወይም ድጋፍ ከፈለጉ ለአካለ ጉዳተኛ መሸጋገሪያ/Disability Gateway እርዳታ መስመር በስልክ1800 643 787 መደወል። ቀጠሮ ሊያቀናጁልዎት ይችላሉ።

አስተርጓሚ ከፈለጉ ለትርጉምና አስተርጓሚ አገልግሎት በስልክ131 450 መደወል እና ወደ አካለ ጉዳተኛ መሸጋገሪያ በስልክ እንዲደወል ይጠይቋቸው።

በአሁን ጊዜ የጤና ችግር ላለባቸው ሰዎች

በአሁን ጊዜ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በCOVID-19 ለሚከሰት በከባድ የመታመም ከፍተኛ ችግር ሊያጋጥማቸው ስለሚችል ክትባትን መውሰድ አለባቸው።

ባለዎት ሁኔታ ላይ በጣም ጥሩ ስለሆነ ክትባት ለእርስዎ መደበኛ ጤና ጥበቃ አቅራቢ ያነጋግሩ።

ክትባትን የት እንደሚወሰድ

COVID-19 ክትባትን ማግኘት የሚችሉት:

 • በCommonwealth ክትባት መስጫ ክሊኒኮች
 • ተሳታፊ በሆኑ የአጠቃላይ ሀኪሞች
 • Aboriginal Controlled Community Health Services
 • በአስተዳደር ክልል እና ተሪቶርይ ክትባት መስጫ ክሊኒኮች፤ እና
 • ተሳታፊ በሆኑ ፋርማሲዎች ላይ ነው።

የአጠቃላይ ሀኪሞች ለክትባት ማስከፈል አይችሉም።

በአቅራቢያዎ ያለን ክትባት መስጫ ክሊኒክ ለማግኘትና ለክትባትዎ ቀጠሮ ለማስያዝ የክትባት ክሊኒክ መፈለጊያን/Vaccine Clinic Finder መጠቀም። በእርስዎ ክትባት ቀጠሮ ጊዜ በስልክ ወይም በአካል ቀርቦ የሚያስተረጉም ከፈለጉ፤ ለትርጉምና አስተርጓሚ አገልግሎት በስልክ 131 450 መደወል።

የMedicare ካርድ ከሌለዎት

Medicare ካርድ ከሌለዎት፤ በነጻ ክትባት ማግኘት የሚችሉት:

 • በCommonwealth ክትባት መስጫ ክሊኒኮች
 • በአስተዳደር ክልል ወይም ተሪቶርይ ክትባት መስጫ ክሊኒኮች
 • ተሳታፊ በሆኑ ፋርማሲስቶች ላይ ነው።

‘ሀይ ኢቫ/Eva’ – በቀላሉ ክትባት ምግኘት

ሰዎች የCOVID-19 ክትባት ቀጠሮን ለማቀናጀት ለመርዳት በቀላሉ ወደ EVA መልሶ መደወያ አገልግሎት ነው። EVA የሚሰራው ከጥዋቱ ሰዓት 7 am እስከ ጥዋቱ 10 am (AEST)፤ በሳምንት ለ 7 ቀናት ይሆናል።

ለCOVID-19 ክትባት ቀጠሮ ለማቀናጀት እርዳታ ከፈለጉ፤ በተክስት መልእክት አድርጎ ‘ለሀይ ኢቫ/Hey EVA’ በስልክ 0481 611 382 መላክ።

መልእክቱን ለ EVA ሲልኩት እንደደረሰ መልሰው የሚጠይቅዎት:

 • ስምዎን
 • የሚፈልጉትን ቋንቋ
 • የሚፈልጉትን ቀንና ሰዓት
 • ለእርስዎ መልሶ ለመደወል ጥሩ የሆነ ስልክ ቁጥርዎን ይሆናል።

COVID-19 ክትባት መውሰድ ቀጠሮ በተመደበው ጊዜ እርስዎን ለመርዳት ከNational Coronavirus Helpline ስልጠና ያገኘ ኦፕሬተር ይደውልልዎታል።

ስለ COVID-19 ክትባቶችና እርዳታዎች በEVA በኩል የሚቀርብ መረጃ እና ምክር:

 • ስለ COVID-19 ክትባቶች መረጃ እና ምክር ማቅረብ
 • በእግር ገብቶ የሚወሰድበት ክሊኒል እንዲያገኙ መርዳት
 • ተገቢ የሆነ የክትባት ቀጠሮ እንዲያገኙ መርዳት
 • በነጻ ከአስተርጓሚ እርዳታ ጋር እንዲገናኙ ማድረግ ነው።

ከእርስዎ COVID-19 ክትባት በፊት

ቀደም ሲል ቀጠሮ ካላስያዙ.

ክሊኒክን ማግኘትና ቀጠሮ ማስያዝ

Medicare ካለዎት፤ ዝርዝር መረጃዎ ወቅታዊ ስለመሆኑ ማጣራት:

ከቀጠሮ ማስያዝዎ በፊት የስምምነት መስጫን ቅጽ እንዲሞሉ ሊጠየቁ ይችላሉ፤ ወይም ለሆነ ሰው ክትባትን እንዲወስድ የሚወስኑ ከሆነ ነው።

ማንበብለስምምነት መስጫ ቅጽ.

ማንበብእድሚያቸው ከ5 እስከ 11 ዓመት ለሆኑ ህጻናት መረጃ እና የስምምነት መስጫ ቅጽን።

ከርስዎ COVID-19 ክትባት በኋላ

ክትባቱን ከወሰዱ በኋላ ምናልባች አልፎ አልፎ የሚፈጠር አለመስማማት አለርጂክን ለመከታተል ቢያንስ 15 ደቂቃዎች ቁጥጥር ይደረጋል። ክትባቱን የሚሰጥዎ ሰው ችግር ከተፈጠረ ወዲያውኑ ምላሽ ለሚሰጥ ስልጠና ያገኘ ነው።

ከCOVID-19 ክትባቶች ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮች በአብዛኛው አነስተኛ እና ከ 1 እስከ 2 ቀናት ውስጥ በራሳቸው ይጠፋሉ። ሊፈጠር በሚችል የተለመዱ ችግሮች የሚካተት:

 • መርፌው በተወጋበት የእጅ ክንድ ላይ ህመም
 • የድካም መንፈስ
 • እራስ ምታት
 • የጅማት ህመም
 • ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለትን ነው።

እንደ ማንኛውም መድሃኒቶች ወይም ክትባቶች አልፎ አልፎ ወይም የማይታወቅ ችግሮች ሊፈጠር ይችል ይሆናል። ከባድ የሚከሰት ችግር አለብኝ ብለው ካሰቡ ለእርስዎ ጤና ጥበቃ ባለሙያ፤ ወይም የአገር አቀፍ ኮሮናቫይረስ እርዳታ መስመርን ያነጋግሩ።

ስልክ 1800 020 080

አስተርጓሚ ከፈለጉ ለአገር አቀፍ ኮሮናቫይረስ እርዳታ መስመር መደወል እና ቁጥር 8’ን መምረጥ።

ክትባት ስለመውሰድ ማስረጃ

የእርስዎን COVID-19 ክትባት መውሰድ ማስረጃ ማግኘት የሚችሉት ለእርስዎ በሽታ መከላከያ ክትባት ታሪክ ጽሁፋዊ መግለጫን በመጠቀም ይሆናል።

ለእርስዎ በሽታ መከላከያ ክትባት ታሪክ ጽሁፋዊ መግለጫን መጠቀም የሚችሉት:

Medicare ካርድ ከሌለዎት፤ ወይም ለmyGov አካውንት መገልገያ ከሌለዎት፤ የእርስዎን በሽታ መከላከያ ክትባት ታሪክ ጽሁፋዊ መግለጫ መጠቀም የሚችሉት:

 • ለእርስዎ ክትባት ላቀረበልዎ አትሞ ቅጂ እንዲሰጥዎ በመጠየቅ
 • ለAustralian Immunisation Register ጥያቄ ማቅረቢያ መስመር በስልክ1800 653 809 (ሰዓት 8 am – 5 pm ከሰኞ እስከ ዓርብ AEST) በመደወል እና በፖስታ አድርገው የእርስዎን ጽሁፋዊ መግለጫ እንዲሉክልዎት በመጠየቅ ነው። በፖስታ ተደርጎ ለመድረስ እስከ 14 ቀናት ሊወስድ ይችላል።

የእርስዎን COVID-19 ክትባት መውሰድ ማስረጃ እንዴት እንደሚያገኙ ለበለጠ መረጃ በድረገጽ Services Australia ላይ ማየት።

ታማኝ ለሆነ መረጃ የት እንደሚኬድ

ታማኝ ከሆኑ ህጋዊ መገልገያ ምንጮች ስለ COVID-19 እና ስለ COVID-19 ክትባት አወሳሰድ ፕሮግራም መረጃ እያገኙ መቆየት ጠቃሚ ነው።

ስለ COVID-19 ክትባቶች ለቀረቡ የተለመዱ ጥያቄዎች መልሶችበ63 ቋንቋዎች ይቀርባል።

መረጃን ማንበብ ስለ COVID-19 በራስዎ ቋንቋ።

መገልገያዎች

Language: 
Amharic - አማርኛ
Last updated: 
13 May 2022