The government is now operating in accordance with the Guidance on Caretaker Conventions, pending the outcome of the 2025 federal election.

ራስዎን እና ሌሎችንም ከ COVID-19 ቫይረስ መከላከል

ኧርስዎም ሆኑ በአካባቢዎ ያሉ ሰዎች ከአደጋ ለመጠበቅ ሊወስዷቸው የሚችሉት እርምጃዎች አሉ።

ክትባት ማግኘት

ከCOVID-19 በሚከሰት ከባድ በሽታን ለመከላከል የCOVID-19 ክትባቶች ተጨማሪ ሀይልን ይሰጥዎታል። ማን ክትባት ለመውሰድ እንደሚገባው ምክሮች የሚያቀርብ የአውስትራሊያ ቴክኒክ አማካሪ ቡድን (ATAGI) ምክርን እንከተላለን።

በእርስዎ ክትባት መውሰድ ጋር ወቅታዊ ሆኖ መቆየት የተሻለ ጥበቃን ይሰጥዎታል።

ክትባት ለመውሰድ ቀጠሮ መያዝ

በሚያስፈልግበት ጊዜ የፊትና አፍ መሸፈኛ ጭምብል ማጥለቅ

የፊትና አፍ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ እርስዎም ሆኑ በዙሪያዎ ያሉትን ሰዎች ከአደጋ ለመጠበቅ ይረዳል።

የፊትና አፍ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ቫይረሶች በአየር ውስጥ እንዳይሰራጩ ያግዳል። ይህም ማለት ቫይረሱን የመያዝ ወይም የማሰራጨት አጋጣሚዎት አነስተኛ ነው ማለት ነው።

የአስተዳደር ክልሎች እና ተሪቶርይ መንግስታት ጭምብል ማድረግ ያለብዎ መቼ እንደሆነ የተለያዩ ደንቦች አሏቸው። የቅርብ ጊዜ ምክር ለማግኘት የአካባቢዎን ጤና ጥበቃ መምሪያ ድረ-ገጽ ይመልከቱ።

መቼ የፊትና አፍ መሸፈኛ ጭምብል ማጥለቅ ጥሩ ሀሳብ እንደሆነ፡

  • የህዝብ ትራንስፖርትን፣ ክሊኒኮችንና ሆስፒታሎችን ጨምሮ በቤት ውስጥ በሚገኙ የህዝባዊ ቦታዎች
  • ከሌሎች በአካል መራቅ ሳይችሉ
  • አዎንታዊ ምርመራ አድርገው ወይም COVID-19 ያለብዎ ከመሰለ፤ እንዲሁም ከሌሎች ሰዎች ጋር ከሆኑ ነው።

የፊት ጭምብልን በአግባቡ ለመጠቀም ማድረግ ያለብዎት፡

  • እጆችዎን ከመልበስዎ ወይም ከማውለቅዎ በፊት መታጠብ ወይም ማጽዳት
  • አፍንጫዎንና አፍዎን የሚሸፍን ከመሆኑም በላይ ከአገጭዎ በታች የተንቆጠቆጠ መሆኑን ያረጋግጡ
  • ጭምብልዎን በሚያጠልቁበት ወይም በሚያስወግዱበት ጊዜ ፊት ለፊት ያለውን ጭምብል ከመንካት መቆጠብ
  • በቦታው አስቀምጥ – በአንገትዎ ወይም በአፍንጫዎ ስር አታንጠልጥለው
  • በእያንዳንዱ ጊዜ አዲስ ነጠላ የአጠቃቀም ጭምብል ይጠቀሙ
  • እንደገና ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ጭምብሎችን ከተጠቀሙ በኋላ ማጠብና ደረቅ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ።
Date last updated:

Help us improve health.gov.au

If you would like a response please use the enquiries form instead.