COVID-19 ክትባትን ከወሰዱ በኋላ

የCOVID-19 ክትባትዎን ከወሰዱ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ማወቅ፤ ይህም የክትባት ምስክር ወረቀት ሰርቲፊኬትዎን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል፣ ደህና ሆኖ ለመቆየት ምን ማድረግ እንዳለብዎት እና የተፈጠረ ችግር ካለዎት ምን መደረግ እንዳለበት ለማወቅ መፈተሽ።

በሽታ የመከላከል አቅም ለመገንባት ጊዜ ይጠይቃል

ክትባትን ከወሰዱ በኋላ ሰውነትዎ የበሽታ መከላከል አቅምን ለማዳበር ጊዜ ይወስድበታል።

ይህ የመረጃ አቅርቦት/infographic የእርስዎን COVID-19 ክትባት መቼ ማግኘት እንደሚቻል እና የትኞቹን ክትባቶች እና መጠን/doses መውሰድ እንደሚመከር ይዘረዝራል።

አንደኛ የመጀመሪያ ጊዜ ደረጃ መጠን/dose ክትባትዎን ከወሰዱ በኋል ከ12 ቀናት ገደማ በኋላ በከፊል የመከላከያ አቅም ያገኛሉ። ሁለተኛው የመጀመሪያ ጊዜ ደረጃ መጠን/dose ክትባትዎን ከወሰዱ በኋላ ሰውነትዎ ጠንካራ የበሽታ መከላከያ (immunity) እንዲፈጥር ያበረታታል። ከባድ የበሽታ መከላከል አቅም ድክመት ላላቸው ሰዎች ሶስተኛውን መጠን/dose ክትባትን መውሰድ ያስፈልጋል።

ጠንካራ የመከላከያ ሀይል ከማግኘትዎ በፊት የማበረታቻ መጠን/dose ክትባትን ከመውሰዱ በኋላ ከ7 እስከ 14 ቀናት ይፈጃል።

ስለ ለማበረታቻ መጠን/booster doses ክትባቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሞክር።

መከላከያ አቅም እስከ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ

COVID-19 ክትባቶች ከባድ ሕመም፤ ሆስፒታል ከመግባት እና ከሞት ለመከላከል በጣም ጥሩ በሆነ ሁኔታ እየሰሩ ናቸው። ይሁን እንጂ በበሽታ ከመያዝ ውጤታማነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ይሄዳል። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ተመራማሪዎች እንደሚከተለው ይገልጹታል፡

  • መከላከያ ጥበቃ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ
  • በየዓመቱ እንደ የማበረታቻ መጠን/doses ክትባቶች የሚያስፈልግዎ ከሆነ ነው።

በአሁኑ ጊዜ፣ COVID-19 ክትባትዎን ከወሰዱበት ጊዜ አንስቶ 6 ወር ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ያለክፍያ በነጻ የማበረታቻ መጠን/dose ክትባትን መውሰድ ይችላሉ።

ስለ የማበረታቻ መጠን/doses ክትባቶች በተጨማሪ ማወቅ።

የ COVID-19 ዲጂታል ሰርተፊኬት/ምስክር ወረቀት ማግኘት

የ COVID-19 ክትባት የመጀመሪያ ጊዜ ደረጃ ክትባትዎን ከጨረሱ በኋላ ለክትባት የምስክር ወረቀት ማግኘት ይችላሉ። ሁለተኛ መጠን/dose ክትባትን ከወሰዱ እስኪደርስዎ 2 ሳምንት ገደማ ሊፈጅብዎት ይችላል።

ለ COVID-19 ክትባትዎ መውሰድ ማረጋገጫ ማግኘት የሚችሉት የእርስዎን በሽታ መከላከያ ክትባት ታሪክ ጽሁፋዊ መግለጫ በማግኘት ነው።

የእርስዎን በሽታ መከላከያ ክትባት ታሪክ ጽሁፋዊ መግለጫ ማግኘት የሚችሉት፡

የ Medicare ካርድ ከሌለህ ወይም myGov አካውንት መጠቀም ካልቻሉ ከበሽታ መከላከያ ክትባት ታሪክ ጽሁፋዊ መግለጫን ማግኘት የሚችሉት፡

  • የክትባት አቅራቢዎን አንድ ቅጂ እንዲያትምልዎት መጠየቅ
  • የአውስትራሊያ በሽታ መከላከያ ክትባት ምዝገባ ሬጅስትራር ጥያቄ ማቅረቢያ መስመር በስልክ 1800 653 809 (ከጥዋቱ 8 am እስከ ከሰዓት በኋላ 5 pm ከሰኞ እስከ ዓርብ AEST) በመደወል ጽሁፋዊ መግለጫዎን በፖስታ እንዲላክልዎት መጠየቅ። በፖስታ ቤት ለመድረስ እስከ 14 ቀናት ሊፈጅ ይችላል።

የCOVID-19 ክትባትዎን ማስረጃ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት በአገልግሎት አውስትራሊያ ድረገጽ (Services Australia website) ላይ ይመልከቱ።

የጎንዮሽ ችግሮች

በክትባቶች ሳቢያ የሚከሰት ከባድ ወይም አለመስማማት አለርጂክ እምብዛም አይታዩም። አብዛኛውን ጊዜ ክትባት ከወሰዱ በኋላ በ15 ደቂቃ ውስጥ ይከሰታሉ።

ክትባት ከወሰዱ በኋላ ቢያንስ ለ15 ደቂቃ ክትትል ይደረግልዎታል። ክትባቱን የሚሰጥዎት ሰው ወዲያውኑ ለተፈጠረው ምላሽ እንዲሰጥ ሥልጠና ተሰጥቷል።

ክትባትን በመውሰድ ሳቢያ የሚከሰት የጎንዮሽ ችግር ካለብዎት

አብዛኞቹ በክትባት ሳቢያ የሚከሰቱ ችግሮች መካከለኛ እንደሆኑና በጥቂት ቀናት ውስጥ ይጠፋሉ። አልፎ አልፎ በክትባት ሳቢያ የሚከሰቱ ችግሮች የከፋ ሊሆን ይችላል።

በክትባት ሳቢያ ለሚከሰቱ ችግሮች እርዳታ መጠየቅ እንዳለብዎት በበለጠ መማር።

በጤና መመርያ በሽታ ምልክት ምርመራ በማድረግ ማጣሪያ ስለሚያጋጥምዎ የህመም ምልክቶች መመርመር ይችላሉ። 

ሊከሰት በሚችል ችግር ያሉትን የበሽታ ምልክቶች ማጣራት

በተጨማሪም በስልክ 1800 020 080 አድርጎ ለአገር አቀፍ ኮሮናቫይረስ እና COVID-19 የክትባት እርዳታ መስመር መደወል ይችላሉ።

ስለ አጠቃላይ ክትባት ደህንነት እና ሊከሰት ስለሚችሉ ችግሮች በበለጠ ማወቅ ወይም ከተወሰኑ የጎንዮሽ ችግሮች ጋር የተዛመድን ማየት፡

ለተጠረጠረ ሁኔታ ምላሽ ወይም የጎንዮሽ ችግርን ሪፖርት

ለተጠረጠሩ የጎንዮሽ ችግሮች እና ምላሾችን ሪፖርት ማድረጉ ታዲያ የክትባት ደህንነትን ለመከታተል ይረዳናል። እያንዳንዱ ሪፖርት ጠቃሚ ከመሆኑም በላይ የሚወሰድ ክትባት ደህንነቱ አስተማማኝ እንዲሆን ይረዳል።

እርስዎም ሆኑ ሀኪም ከሚወስዱት ክትባት የተዛመደ ችግር ካለ ወይም የጎንዮሽ ችግር ካጋጠምዎት እባክዎ ሪፖርት ያድርጉ።

ሀኪምዎን ለህክምና ጥራት አስተዳደር (TGA) ሪፖርት እንዲያደርግልዎት መጠየቅ ይችላሉ።

ወይም የጎንዮሽ ችግሮችን ራስዎ ሪፖርት ማድረግ የሚችሉት፡

በክትባት ሳቢያ የተከሰተ ችግር ካጋጠምዎት በእኛ COVID-19 የክትባት ጉዳት ማካካሻ መርሃ ግብር መሰረት ካሳ ለማግኘት ብቃት ሊኖርዎ ይችላል።

Last updated:

Help us improve health.gov.au

If you would like a response please use the enquiries form instead.