መቼ ምርመራ ማድረግ
ማንኛውም የ COVID-19 በሽታ ምልክቶች ካለዎት መመርመር አለብዎት።
የ COVID-19 ምርመራዎች ዓይነቶች
COVID-19 ቫይረስ ካለዎት መለየት የሚችሉ 2 ዓይነት ምርመራዎች አሉ።
- ፈጣን የአንቲጀን በራስ ምርመራ ማድረግ (RATs)
- ፖሊመራሰ/polymerase ሰንሰለት ምላሽ (PCR, ወይም RT-PCR)
COVID-19 ምርመራ እንዴት እንደሚሰራ በበለጠ መማር።
ምርመራ የት ማድረግ እንደሚቻል
እርስዎ በቤት ውስጥ RAT ምርመራ ማድረግ ይችላሉ።. ትላልቅ የገበያ አዳራሾችንና አንዳንድ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎችን ጨምሮ ፋርማሲዎች ወይም ቸርቻሪ ነጋዴዎች እነዚህን መመርመሪያዎች ይሸጣሉ።
መመሪያውን በሚከተለ ለማንበብ፡
የ PCR ምርመራን ለማግኘት እንዲላኩ ለሪፈራል የእርስዎን አጠቃላይ ሀኪም/GP ማነጋገር ወይም በእርስዎ አስተዳደር ግዛት ወይም ተሪቶርይ ውስጥ የሚገኙ ከሆነ COVID-19 ምርመራ ክሊኒክ መጎብኘት ይኖርብዎታል።
በአቅራቢያዎ ለሚገኙ የምርመራ ማካሄጃ ክሊኒኮች ዝርዝር የአካባቢዎ ጤና ጥበቃ መምሪያን ይጎብኙ።
Date last updated: