የረጅም ጊዜ COVID

COVID-19 ያለባቸው አብዛኞቹ ሰዎች የመጀመሪያ በሽታ ምልክቶች በታዩበት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ያገግማሉ። ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች በበሽታው ምክንያት ለረጅም ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ። ስለ ረጅም ጊዜ COVID እና ቀጣይነት ላላቸው የህመም ምልክቶች እርዳታ ማግኘት የሚችሉት ከየት እንደሆነ ለማወቅ ጥረት ያድርጉ።

ስለ ረጅም ጊዜ COVID

'ረጅም ጊዜ COVID' የሚለው ቃል በጥቅሉ ሁለቱንም ለመግለጽ ያገለግላል፦

  • ቀጣይ የበሽታ ምልክት COVID-19 – ከ 4 ሳምንታት በላይ የሚቆዩ COVID-19 የበሽታ ምልክቶች
  • ከCOVID-19 ሁኔታ/ጉድለት ሲታይ – ከ12 ሳምንታት በኋላ በአማራጭ የምርመራ ውጤት ያልተብራሩ ምልክቶች።

ረጅም ጊዜ COVID በተለያዩ ሰዎች ላይ ሊያቀርብ የሚችል ሲሆን የበሽታው ምልክቶች ከቀላል እስከ ከባድ ሊታዩ ይችላሉ።

ረጅም ጊዜ የCOVID በሽታ ምልክቶች

ከረጅም ጊዜ COVID ጋር በጣም የተለመዱ የበሽታ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፡

  • ድካም መንፈስ (ድካም)
  • የትንፋሽ እጥረት
  • የማስታወስ ችሎታዎና ትኩረት ችግር ('የአንጎል ብዥታ')።

ሌሎች የበሽታ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፡

  • የልብ ትርታ መጨመር፣ የደረት ህመም ወይም መጨናነቅ
  • ሳል
  • የጣእም ወይም ሽታ ስሜት መለዋወጥ
  • የአጥንት መገጣጠሚያ እና የጡንቻ ህመም
  • ፒንስ/pins እና መርፌዎች
  • እንቅልፍ የመተኛት ችግር (እንቅልፍ ማጣት)
  • የስሜት መለዋወጥ (ጭንቀት፣ መነጫነጭ ወይም የመንፈስ ጭንቀት ድባቴ መጨመር)
  • መደንዘዝ
  • እራስ ምታት
  • ዝቅተኛ-ክፍል ትኩሳት
  • የቆዳ ሽፍታ፤ የፀጉር መርገፍ
  • የማቅለሽለሽ ስሜት፣ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት ህመም፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት።

በልጆች ላይ የበሽታው ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፡

  • የስሜት መለዋወጥ ምልክቶች
  • የድካም ስሜት
  • እንቅልፍ የማጣት ችግር።

ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የCOVID አደጋ ምክንያቶች

ለረጅም ጊዜ COVID በሰዎች ላይ የመከሰት እድሉ ሰፊ የሚሆነው፡

  • ላልተከተቡ
  • ከ COVID-19 ጋር ከባድ ህመም ለነበረበት፤ ከእነዚህም መካከል ሆስፒታል ለገቡት ወይም ከፍተኛ እንክብካቤ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ያካትታል
  • ከCOVID-19 በፊት እንደ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ሥር የሰደደ የሳንባ በሽታ፣ የስኳር በሽታና ከልክ ያለፈ ውፍረት የመሳሰሉ ከበስተጀርባ ያሉ ችግሮች ወይም በሽታዎች ከነበሩባቸው።

ለረጅም ጊዜ የቆየ COVID ህክምና ማግኘት

COVID-19 ከያዝዎ በኋላ ቀጣይነት ያላቸው የበሽታ ምልክቶች ካሉዎ የህክምና ምርመራ ለማድረግ ሀኪምዎን ማነጋገር ይኖርብዎታል።

ለረጅም ጊዜ COVID ምርመራ የለም። ሀኪምዎ ስለ በሽታ ምልክቶችዎና በህይወትዎ ላይ ስለሚያድርጉት ተጽእኖ ይፈጥራል። የበሽታው ምልክቶች ሊታዩብዎ የሚችሉ ነገሮችን ለይተው ለማወቅና ሌሎች ችግሮችን ለማስወገድ አንዳንድ ምርመራዎችን ሊያቀርቡልዎት ይችላሉ።

ለረጅም ጊዜ COVID ለማከም አንድም ህክምና ወይም መድሃኒት የለም። ሀኪምዎ ስለሚያስፈልግዎይ እንክብካቤና ድጋፍ ያነጋግርዎታል። ስለዚህ ጉዳይ ምክር ሊሰጡዎት የሚችሉት፡

  • በቤትዎ ውስጥ የበሽታ ምልክቶችዎን መከታተል እና ማስተካከል፣ ለምሳሌ የሽታ ምልክት ማስታወሻ መመዝገቢያ በመጠቀም
  • የህክምና ክትትል ሊያስፈልጋቸው የሚችሉ (እንደ አዳዲስ ወይም እየተባባሱ ከሚሄድ የህመም ምልክቶች) እና እነዚህ ምልክቶች ካጋጠመዎት የት ክትትል ማድረግ ይኖርብዎታል
  • ከCOVID-19 በኋላ ባሉት ሳምንታት እና ወራት ውስጥ ምን እንደሚጠበቅ
  • እንደ አመጋገብ፣ አካላዊ እንቅስቃሴና ምክር የመሳሰሉትን የአኗኗር ዘይቤዎች የሚረዱ ድጋፍዎች።

የበሽታው ምልክቶች በህይወትዎ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እያስከተለ ከሆነ የህመም ምልክቶችዎን ለመቆጣጠርና ከበሽታው ለማገገም ወደሚረዳዎ ልዩ ባለሙያ/ስፔሻሊስት ወይም የማገገሚያ አገልግሎት መላክ ይችላሉ።

ከረጅም ጊዜ COVID ማገገም

እያንዳንዱ ሰው ከህመሙ የሚላቀቅበት ጊዜ እንደሚለያይ እና የበሽታው ምልክቶችም በጊዜ ሂደት ሊለያዩ ይችላሉ። አብዛኞቹ ሰዎች ከ3 እስከ 4 ወራት ውስጥ ያገግማሉ። ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች የበሽታው ምልክቶች ረዘም ላለ ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ።

ራስውን ከረጅም ጊዜ COVID ስለመከላከል

ለረጅም ጊዜ COVIDን ለመከላከል ከሁሉ የተሻለው መንገድ እራስዎን ከቫይረስ ብክለት መከላከል

በእርስዎ COVID-19 ክትባት መውሰድ ጋር ወቅታዊ ሆኖ ቆይታ COVID-19 ኢንፌክሽንን ለመከላከል እና ከባድ ህመም ለመከላከል ሊረዳ ይችላል። ክትባትን የወሰዱ ሰዎች ክትባት ካላገኙ ሰዎች ጋር ሲወዳደሩ ለረጅም ጊዜ COVID መያዝ ሪፖርት የተደረገ አጋጣሚዎች አነስተኛ ነው።

የመንግስት ምላሽ

በመስከረም/September 1 ቀን 2022 ዓ.ም ከጤና እና ከእድሜ ክልል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፤ በፓርላማ አባል Hon Mark Butler MP ከተጠቀሰ በኋላ የጤና ሃውስ ቋሚ ኮሚቴ የአረጋውያን እንክብካቤ እና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ለረጅም ጊዜ COVID እና በተደጋጋሚ COVID-19 ልርሚከሰት ብክለት ኢንፌክሽኖች ሪፖርት ያደርጋሉ።

ጊዜያዊ ሪፖርትን ያንብቡ።

ለበለጠ መረጃ

Date last updated:

Help us improve health.gov.au

If you would like a response please use the enquiries form instead.