ከ COVID-19 ከባድ ህመም ወይም ሞት የተሻለ ጥበቃ ለማግኘት በእድሜዎ ወይም በግላዊ ጤናዎ የሚያስፈልግዎትን ለተፈቀደ የክትባት መጠን በሙሉ ማግኘት ይኖርብዎታል። ይህን ጥበቃ ለማስጠበቅ የማበረታቻ ክትባቶችን አስፈላጊ ናቸው።
የማበረታቻ መጠን/doses ክትባቶች ለሁሉም ሰው ያለ ክፍያ በነጻ ይሆናል።
ስለ ማበረታቻ መጠን/doses ክትባቶች መረጃም በራስዎ ቋንቋ ይገኛል።
የማበረታቻ መጠን/doses ክትባት
ሁሉም ጎልማሳ አዋቂዎች ካለፈው COVID-19 ማበረታቻ ክትባት ከወሰዱ 6 ወራት ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ወይም የተረጋገጠ ብክለት ኢንፌክሽን ካለ (የትኛውም ቀድሞ ቢከሰትም) ከ COVID ከባድ ሕመም ተጨማሪ መከላከያ ክትባት ማግኘት ይችላሉ።
ይህም በተለይ ለከባድ ህመም ተጋላጭነት ከፍተኛ ለሆኑ ሰዎች ይመከራል። በዚህ የሚካተት፡
- እድሜው 65 ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆነ እያንዳንዱ ሰው
- እድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆነ እና የህክምና ችግር፤ የአካል ጉዳት ወይም ውስብስብ የጤና ፍላጎቶች ላለባቸው ሰዎች በሙሉ።
ከ5 እስከ 17 ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች፤ በከባድ ህመም የሚዳርጉ የጤና ችግሮች ያሉባቸዉ የማበረታቻ ክትባት ማግኘት ሲችሉ፤ ይህም ከእነሱ በሽታ መከላከያ ክትባት አቅራቢ ጋር በግለሰብ ደረጃ በተደረገ የአደጋ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የመጨረሻ የበሽታ መከላከያ ክትባት ወይም COVID-19 ብክለት ኢንፌክሽኑ ካለፈ 6 ወር ከሞላዉ የማበረታቻ ክትባት ሊያገኙ ይችላሉ።
በዚህ ጊዜ እድሜያቸው 18 ዓመት ወይም ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችና በጉርምስና እድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ለከባድ COVID-19 ሕመም መንስኤ የሌላቸው ሰዎች የማበረታቻ ክትባት መውሰድ አይመከርም።
ሁሉም ክትባቶች በአውስትራሊያ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀደላቸው ሲሆን ከ COVID-19 ከባድ በሽታ በጣም ጠንካራ ጥበቃ ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ፤ ይሁን እንጂ Omicron-specific bivalent ክትባቶች የማበረታቻ ክትባት እንዲሆኑ ይመረጣል።
የእርስዎ የመጨረሻ COVID-19 ክትባትን የወሰዱበት ቀን በእርስዎ COVID-19 ዲጂታል የምስክር ወረቀት ላይ ነው።
ለማበረታቻ መጠን/doses ክትባት እንዴት ቀጠሮ እንደሚቀናጅ
ለማበረታቻ መጠን/dose ወይም የክረምት የማበረታቻ መጠን/dose ክትባት ቀጠሮ ለማስያዝ COVID-19 ክሊኒክ ማውጫን ወይም 'ሄይ ኢቫ' – Easy Vaccine Access ይጠቀሙ።
ኢቫ/ EVA ሰዎች ለCOVID-19 ክትባት ቀጠሮ በማስያዝ ለመርዳት ቀላል የመልሶ ጥሪ አገልግሎት ነው።
የCOVID-19 ክትባት ቀጠሮ ለማስያዝ እርዳታ ካስፈለገ ኤስኤምኤስ/SMS 'ሄይ ኢቫ'/Hey EVA’ አድርጎ ወደ 0481 611 382 መላክ።. ከአህጉራዊ ኮሮናቫይረስ እርዳታ መስመር የሰለጠነ የስልክ ጥሪ ወኪል የCOVID-19 ክትባትዎን ቀጠሮ ለመያዝ ይረዳዎታል።
ለእድሜ አንጋፋ አረጋውያን እንክብካቤ መኖሪያ ቤት የማበረታቻ ክትባት ፕሮግራም
በአረጋውያን መኖሪያ ተቋማት መገልገያዎች ውስጥ የማበረታቻ ክትባት ፕሮግራም እየተካሄደ ነው። በመኖሪያ ቤት አረጋውያን እንክብካቤስለ COVID-19 ማበረታቻ መጠን/ dose ክትባት መስጫ ፕሮግራም በበለጠ ማንበብ።
አካለ ጕዳተኛ ለሆኑ ሰዎች የማበረታቻ ክትባት ፕሮግራም
በጋራ ተዳብሎ መኖሪያ ቤት ለሚገኙ የአካል ጉዳተኞች የማበረታቻ ክትባት ፕሮግራም እየተሰራ ነው። ስለ COVID-19 የማበረታቻ መጠን/dose ክትባት ፕሮግራም ለአካል ጉዳተኞች በጋራ ተዳብሎ መኖሪያ ቤት ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች በበለጠ መማር።
ደህንነቱ የተጠበቀ የ COVID-19 የማበረታቻ መጠን/dose ክትባቶች
የማበረታቻ መጠን/dose ክትባት በኋላ የሚከሰቱ የተለመዱና ቀላል የሆኑ የጎንዮሽ ጉዳቶች ከመጀመሪያዎቹ 2 መጠን/dose ክትባቶች በኋላ ከሚያስከትሉት የጎንዮሽ ጉዳት ጋር ይመሳሰሉ።
ስለ COVID-19 የክትባት ደህንነት እና ሊከሰት የሚችል ችግሮች መረጃን ማየት።