COVID-19 እና ጉዞ

ከአደጋ ለመጠበቅ የሚወስዷቸውን የጉዞ መስፈርቶችና እርምጃዎች ለማወቅ መሞክር።

በአውስትራሊያ ውስጥ የአካባቢ ጉዞ

ጉዞን በተመለከተ መረጃ ለማግኘት በአካባቢው የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤቶች ድረገፆች ላይ ማጣራት፦

ወደ ውጭ አገር መጓዝ

በአውስትራሊያና በውጭ አገር ለጤና አደጋ ማጋለጡን COVID-19 ቀጥሏል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚጓዙበት ጊዜ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማጥለቅና ክትባት መውሰድ እንዳለብን አጥብቀን እንመክራለን። የሳልንና የእጅ ንጽህናን መጠበቅ እንዲሁም በተቻለ መጠን ከሌሎች ሰዎች መራቅ ይኖርብዎታል።

አንዳንድ አገሮች፣ የአውሮፕላኖችና የመርከብ ኦፕሬተሮች COVID-19 የጉዞ መስፈርትን ማሟላት ሊኖርባቸው ይችላል። ከእነዚህም መካከል በበረራዎ ወይም በመርከብዎ ላይ ከመሳፈርዎ በፊት ከጉዞ በፊት ምርመራ ማድረግ ሊያስፈልግዎ ይችላል። የሁለቱንም መግቢያ መስፈርት ማጣራት፦

  • የምትጓዙበት አገር ወይም ለመሸጋገሪያ የምታልፉት አገር

  • የአውሮፕላን ወይም የመርከብ ኦፕሬተር መስፈርቶች።

መገልገያዎች

አውስትራሊያውያን ወደ አገራቸው ስለመመለስ

የአውስትራሊያ ድንበሮች የተከፈቱ ናቸው፣ እናም በAustralian Government/አውስትራሊያ መንግሥት የሚከተሉትን ብቃቶች አለማሟላት፡

  • ወደ አውስትራሊያ ሲደርሱ በምርመራ ውጤት COVID-19 እንደሌለብዎት ማስረጃ መስጠት
  • COVID-19 ክትባት መውሰድ ማስረጃ ማቅረብ
  • ይህ የሚበረታታ ቢሆንም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማጥለቅ።

የጉዞ ኢንሹራንስ

ከCOVID-19 ጋር በውጭ አገር የምትታመም ከሆነ የጉዞ ኢንሹራንስ በጣም አስፈላጊ ነው። የኢንሹራንስዎ የሚከተሉትን ነገሮች እንደሚጨምር ማረጋገጥ፦

  • የጉዞ መዳረሻዎች
  • ለ COVID-19 የሚያካትት
  • እንደ ጉዞ የአስተናጋጅ ኢንሹራንስ ያሉ ሌሎች ተጨማሪ ነገሮች።

በተጨማሪም አንዳንድ ቦታዎች ተጓዦች ወደ ውስጥ አገር ለመግባት የሚያስችል የጉዞ ኢንሹራንስ እንዲይዙ ይጠይቃሉ።

በመርከብ ጉዞ

በመርከብ ጉዞ ለምትሄድበት ቦታ ወቅታዊ የሆኑ የጉዞ ብቃዎችን ለማወቅ የጉዞ ከአቅራቢዎ ጋር ማረጋገጥ።

ክትባት መውሰድ

ተጓዦች በጉዞ መርከብ ላይ ሲሳፈሩ ክትባት እንዳገኙ የሚጠይቅ ነገር በ Australian Government የለም። ይሁን እንጂ እንዲህ እንመክራለን፡

  • COVID-19 ክትባትን መውሰድ ከባድ ሕመም እና ረጅም ጊዜ የሚቆይ COVID-19 በክትባት ካልታከሙ ለከፍተኛ አደጋ እንደሚጋለጡ
  • ካልተከተቡ በመርከብ ያለዎትን ጉዞ እንደገና ግምት ውስጥ ማስገባት።

በመርከብ ጉዞ ላይ የተከሰተው ወረርሽኝ

የመጓጓዣ መርከቦች ከሌሎች የጉዞ ዓይነቶች ጋር ሲወዳደሩ በበሽታ የመያዝ አጋጣሚያቸው ከፍተኛ ነው። COVID-19፣ ኢንፍሉዌንዛና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች በቅርብ አካባቢ በሚኖሩና ማሕበራዊ ግንኙነት በሚያደርጉ ሰዎች መካከል በቀላሉ ይሰራጫሉ።

በመርከብ ጉዞዎ ላይ COVID-19 ወረርሽኝ ቢከሰት, ሊያስፈልግዎ የሚችል፡

  • በመርከብ ላይ ተገልሎ እንዲቆይ
  • ከባቡር ላይ መውረድ እና በያላችሁበት ስተዳደር ግዛት ወይም ተሪቶርይ ወይም አገር ውስጥ ያሉትን የአካባቢ ደንብ መከተል ነው።

ከመጓዝዎ በፊት በጉዞ ላይ ቀልጣፋ ተጓዥ/Smartraveller ምክሮችን ይመልከቱ ስለ COVID-19 የደህንነት ፕሮቶኮሎቻቸው የተወሰነ መረጃ ለማግኘት የጉዞ ወኪልዎን ወይም የመርከብ ጉዞ ኦፕሬተርዎን ያነጋግሩ።

የአስተዳደር ክልል እና ተሪቶርይ መንግስታት በአውስትራሊያ የመርከር ጉዞ ዝውውር የሚደግፉ የጤና ፕሮቶኮሎችን ያዘጋጃሉ እንዲሁም ያሻሽላሉ።

በተጨማሪም የመርከብ ጉዞ/ክሩዝ ኢንዱስትሪ ፕሮቶኮሎች በጉዞ ላይ ባሉ መርከቦች ላይ COVID-19 ቫይረስ የመተላለፍን አደጋ ለመቀነስ ይረዳሉ፡ ከእነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

  • ለመንገደኞች ክትባት መውሰድ መስፈርቶች
  • ወረርሽኙን የመቆጣጠር እቅድ
  • COVID-19 የደህንነት እቅድ።

ዓለም አቀፍ ተጓዦች ወደ አውስትራሊያ

የአውስትራሊያ ድንበሮች የተከፈቱ ናቸው፣ እናም በ Australian Government የሚከተሉትን ብቃቶች የማያሟሉ፡

  • ወደ አውስትራሊያ ሲደርሱ በምርመራ ውጤ COVID-19 ቫይረስ እንዳልተገኘ ማስረጃ መስጠት
  • COVID-19 ክትባት መውሰድ ምስረጃ ማቅረብ
  • የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብልን ማጥለቅ ቢሆንም የሚበረታታ ነው።

ስለ አውስትራሊያ መግባት እና መውጣት ተጨማሪ ማወቅ።

Date last updated:

Help us improve health.gov.au

If you would like a response please use the enquiries form instead.