ኮቪድ/COVID-19 ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው
ህክምናን በጥሩ አስተዳደር/Therapeutic Goods Administration (TGA) የአንድን ክትባት ደህንነት በጥንቃቄ የሚገመግም የክትባት ፈቃድ አሰራር ሂደት አለው።
TGA የCOVID-19 ክትባት ደህንነትን የሚከታተለው፡
- የጎንዮሽ ጉዳቶችን ጥሬ መረጃ ማሰባሰብ እና ሪፖርት በማድረግ
- እውቀትን ለማጋራት ከዓለም አቀፍ ተቆጣጣሪዎች ጋር አብሮ በመስራት
- ደህንነትን በመከታተል
- በእያንዳንዱ ቡድን ላይ ማጣራት የጥራት ደረጃዎችን በማሟላት ይሆናል።
በእርግዝና ወቅት ደህንነት
የአውስትራሊያ ቴክኒክ አማካሪ ቡድን ስለ በሽታ መከላከያ ክትባት (ATAGI) በእርግዝና ወቅት COVID-19 ክትባቶችን መጠቀምን በተመለከተ የሚከተለውን ምክር ሰጥቷል፡
- እርጉዝ ከሆኑ በማንኛውም የእርግዝና ወቅት የ Pfizer ክትባት ማግኘት ይችላሉ።
- እርጉዝ ለመሆን እየሞከሩ ከሆነ ክትባት ለመውሰድ መዘግየት የለበትም ወይም ክትባት ከወሰዱ በኋላ ከማርገዝ መቆጠብ አያስፈልግዎትም።
- እርጉዝና ጡት የሚያጠቡ ከሆነ የ Pfizer ክትባት ድህንነቱ አስተማማኝ መሆኑን እውነተኛ ዓለም ማስረጃዎች ያሳያሉ።
- የ Pfizer ክትባት ማግኘት ካልቻሉ የ Novavax ክትባት ለእርስዎ ትክክል ስለመሆኑ ሀኪምዎን ማነጋገር ይችላሉ።
- እርጉዝ ከሆኑና ክትባት ያልወሰዱ ከሆነ በCOVID-19 ምክንያት በከባድ ህመም የመያዝ አጋጣሚዎ ከፍ ያለ ነው። በተጨማሪም የተጠነሰው ልጃቹ ያለ እድሜው (ከ37 ሳምንታት እርግዝና በፊት) የመውለድ አጋጣሚ ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል።
- COVID-19 ክትባትን መውሰድ በእርግዝና ወቅት ለህጻኑ ጸረ እንግዳ አካላትን በእምብርት ማስተላለፍ (በእርግዝና ወቅት) ወይም በእናት ጡት ወተት (ጡት በሚጠባበት ጊዜ) ለህጻናት መከላከያን መስጠት ይችል ይሆናል።
ስለ እርግዝና፤ የእናት ጡት ማጥባት እና COVID-19 ክትባቶች ተጨማሪ መረጃ መፈለግ።
በክትባት ሊከሰት የሚችል ችግሮች
የTGA ሪፖርት እንደሚለው አብዛኞቹ የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከለኛ እንደሆኑ እና በሁለት ቀናት ውስጥ ይጠፋል።
AusVaxSafety ሰዎች ከ COVID-19 ክትባቶች በኋላ የጎንዮሽ ጉዳት ያጋጥማቸዋል ወይስ አያጋጥማቸውም የሚለውን እንደሚከታተል ነው። በአውስትራሊያ ውስጥ ያላቸው ጥሬ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፡
- ከግማሽ በላይ ተሳታፊዎች ምንም የጎንዮሽ ችግር ጉዳት ሪፖርት አልቀረበም (ወደ 55% ገደማ)
- ከግማሽ በታች ሪፖርት የሚያሳየው ማንኛውም የጎንዮሽ ችግር ጉዳት (ወደ 44% ገደማ)
- ከ1% ያነሰ ሪፖርት የሚያሳየው ከክትባት መውሰድ በኋላ ወደ ሀኪም ወይም በድንገተኛ መታከሚያ ክፍል መሄድ
- ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት በሌሎች አገሮች በክሊኒካል ምርመራና ክትትል ከሚያስከትላቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች ጋር ይመሳሰላሉ።
ክትባት ከመውሰድዎ በፊት ለሚከሰት ማንኛውም ለጎንዮሽ ችግር ጉዳቶች መዘጋጀት አያስፈልግዎም።
ለእያንዳንዱ ክትባት ሊያስከትሉ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ማየት፡
መቸ እርዳታ ስለሚጠየቅ
የሚከተሉት ምልክቶች ካለብዎት በተቻለ ፍጥነት ሀኪምዎን ያነጋግሩ ወይም በቀጥታ ወደ ሆስፒታል መሄድ፡
- ከባድ ወይም ያልተጠበቀ ነው ብለው ያሰቡት ችግር ምላሽ
- የትንፋሽ እጥረት
- የደረት ህመም
- የእግርዎ ማበጥ
- የማይጠፋ የሆድ እቃ ህመም
- የማይጠፋ ከፍተኛ የራስ ህመም
- የክትባት መርፌ በተወጉበት ቦታ ቀደም ሲል ያልነበረ በቆዳ ያሉ ጥቃቅን ነጠብጣቦች።
የተጠረጠረውን የጎንዮሽ ችግር ጉዳት ወይም ችግር ምላሽ ሪፖርት ማድረግ
የጎንዮሽ ጉዳት ወይም ችግር ምላሽ እንዳለዎት ከተጠራጠሩ ጉዳዩን በራስዎ ወይም በሀኪም አማካኝነት ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ከ COVID-19 ክትባት ጋር የተያያዙ ጥርጣሬ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሪፖርት ለማድረግ የበለጠ መረጃ ማግኘት።
የማካካሻ ገንዘብ አሰራር መርሃ ግብር
አልፎ አልፎ የሚከሰት ችግር ካጋጠመዎት በእኛ COVID-19 ክትባት ጉዳት የማካካሻ መርሃ ግብር መሰረት ካሳ ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
በቀጣይ ስለመከታተል
ክትባቶች ከተፈቀደላቸው በኋላም እንኳ TGA በመላ አገሪቱ የሚገኙ ክትባቶችን መከታተሉን ቀጥሏል።
ለደህንነት አደጋ ሊያጋልጥ የማይችል ከሆነ TGA በተቻለ ፍጥነት ለጤና ጥበቃ ተቋማትና ለማህበረሰቡ መረጃ ይሰጣል።