COVID-19 ክትባቶች እንዴት እንደሚሰሩ

የ COVID-19 ክትባቶች እንዴት እንደሚሰሩ፣ እንዴት እንደሚፈቀድላቸው፣ እንዴት እንደምንጠቀምባቸው እንዴት እንደምንወስን እንዲሁም ተአማኒነት ያለው መረጃ ለማግኘት የት መሄድ እንዳለብን ለማወቅ ሞክር።

በዚህ ገጽ ላይ ያለው መረጃ በአዲስ ATAGI ምክር ተፈላጊነት ባለው ቢቫለንት COVID-19 ክትባቶችን በምርጥ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ሲሆን በቅርቡ ወቅታዊ ይሻሻላል።

በአውስትራሊያ COVID-19 ክትባቶች

በአገር አቀፍ የክትባት ዝርጋታችን ላይ 3 COVID-19 ክትባቶችን እየተጠቀምን ነው።

  1. ኮሚርናቲ (Pfizer)
  2. ስፒክቫክስ (Moderna)
  3. ኑቫክሶቪድ (Novavax)

የክትባት ዓይነቶች

በጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀደ 2 አይነት ክትባቶች አሉ፡

የቬክተር ክትባት AstraZeneca በሀገር አቀፍ የክትባት ዝርጋታ ውሰጥ እንደማይጠቅምና ከዚህ በኋላ አቁሟል።

ስለ በሽታ መከላከል ክትባት ሳይንስ የበለጠ ለማወቅ መማር።

ክትባት መስጠት ምክሮች

ስለ በሽታ መከላከያ ክትባት የአውስትራሊያ ቴክኒካል አማካሪ ቡድን (ATAGI) COVID-19 ክትባቶችን ጨምሮ ስለ ክትባቶች ህክምና አስተዳደር ለAustralian Government ይመክራል።

በምርምር እና በህክምና ምክር ላይ የተመሰረተ በእያንዳንዱ COVID-19 ክትባት አጠቃቀም ላይ ምክር ሀሳቦችን ያቀርባሉ። ይህም በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች የትኞቹን ክትባቶች መውሰድ እንደሚያስፈልግ ይጨምራል።

የAustralian Government ክትባቶችን በተመለከተ ፖሊሲ ውሳኔ በሚያደርግበት ጊዜ የATAGIን ምክር ግምት ውስጥ ያስገባል።

ክትባቶች እንዴት ይሰራሉ

እነዚህ ክትባቶች ሰዎች በጠና እንዳይታመሙ ወይም እንዳይሞቁ፣ ከCOVID-19 ቫይረስ ለመከላከል ይረዳሉ።

ክትባቶቹ በሽታ ተከላካይ ህዋሳትዎ በጠና ከመታመምዎ በፊት ቫይረሱን ለይተው ለማወቅና ለማስወገድ ያሰለጥናሉ። የሰውነትዎ በሽታ ተከላካይ ህዋሳት በጊዜ ሂደት ይህን የመከላከል ሀይል አሰራርን ይገነባሉ።

በCOVID-19 ቫይረስ ከከባድ ህመም ወይም ሞት የተሻለ ጥበቃ ለማግኘት ለእድሜዎ ወይም ለግለሰብ የጤና ፍላጎቶች ለማግኘት የሚመከርዎትን ሁሉንም ክትባቶች ወቅታዊ በሆነ መንገድ መውሰድ ይኖርብዎታል። በCOVID-19 (SARS-CoV-2 ይባላል) የሚያመጣው ቫይረስ በእያንዳንዱ የቫይረስ ቅንጣት ላይ የፕሮቲን ስፓይክስ አሉት። እነዚህ ስፓይክ ፕሮቲኖች ቫይረሱ ከሴሎች ጋር እንዲጣበቅና በሽታ እንዲያመጣ ያስችሉታል።

ክትባቶቹ ለሰውነት የሚረዳው ወደ፡

  • እነዚህ ስፓይክ ፕሮቲኖች ስጋት እንደሆኑ እንገነዘባለን
  • እነዚህ ፕሮቲኖች ያሉት ኮሮናቫይረስ ለመዋጋት ይሆናል።

መጠን/Doses

ATAGI ለእያንዳንዱ እድሜና የህዝብ ቁጥር ቡድን የትኞቹን ክትባቶችና መድሃኒቶች መውሰድ እንደሚመከር አስተዋፅዎ አቅርቧል።

COVID-19 ቫይረስ ካለብዎት ከታወቀበት የCOVID-19 ክትባትን ለመውሰድ ለ6 ወራት መጠበቅ ይኖርብዎታል።

ከባድ በሽታ የመከላከል አቅም ችግር ላለባቸው ሰዎች ስለ ሶስተኛ መጠን/doses ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሞክር።

የማበረታቻ መጠን/doses ክትባቶች

በCOVID-19 ቫይረስ ከከባድ ህመም ወይም ሞት የተሻለ ጥበቃ ለማግኘት ለእድሜዎና ለግለሰብ ጤንነትዎ የሚያስፈልግዎን መድሃኒቶች በሙሉ ማግኘት ይኖርብሃል። ይህን ጥበቃ ለማስጠበቅ የማበረታቻ መጠን/doses ክትባቶች አስፈላጊ ናቸው፡

ስለ ለማበረታቻ መጠን/booster doses ክትባቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሞክር።

ክሊኒክ ማግኘት እና ቀጠሮ ማቀናጀት

ክትባቶች የሚፈቀዱት እንዴት ነው?

የህክምና ጥሩ አስተዳደር/Therapeutic Goods Administration (TGA) ጥንቃቄ የተሞላበት ግምገማ ሂደት ካደረገ በኋላ በአውስትራሊያ ጥቅም ላይ የሚውሉ ክትባቶችን ያጸድቃል።

የ COVID-19 ክትባቶች ጊዜያዊ ተቀባይነት አላቸው።. ይህም ማለት በአውስትራሊያ ህጋዊ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ማለት እንደሆነ፤ ምክንያቱም ቀደም ብሎ መጠቀም ከሚያስከትላቸው አደጋዎች ጥቅሙ ይበልጣል። አምራቹ ስለ ክትባት ደህንነት እና ውጤታማነት መረጃ መሰብሰባቸውን የቀጠሉ ሲሆን ከጊዜ በኋላ ሙሉ ፈቃድ ለማግኘት ያመላክታሉ።

በተጨማሪም TGA ክትባት ደህንነት እና የጎንዮሽ ጉዳቶችን ያለማቋረጥ ይከታተላል።

ባለስልጣን የክትባት መረጃ

ብዙ መረጃ አለ – እና የተሳሳተ መረጃ – ስለ ኮሮናቫይረስ እና ስለ COVID-19 ክትባቶች ወጥቷል።

በእውቀት ላይ የተመሠረተ ምርጫ እንድታደርጉና ወቅታዊ መረጃ እንድታገኙ ለመርዳት ጥሩ ስመ ጥሩ መገልገያ ምንጮችን እንድትጠቀሙ እናበረታታለን።

ስለ COVID-19 ክትባቶች ተደጋጋሚ መረጃ ይቀርባል።

Date last updated:

Help us improve health.gov.au

If you would like a response please use the enquiries form instead.